Tender Detail

Tender Details

  • Company በምዕራብ ጐንደር ዞን የገ/ውሃ ቴ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ
  • Address ጐንደር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 058 33 110 415
  • Website
  • Deadline07 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Educational And Training Equipment And Machinery

በምዕራብ ጐንደር ዞን የገ/ውሃ ቴ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ የፅህፈት መሣሪያ ጋርመንት ኮንስትራክሽን ኤሌክትሮኒክስ የግንባታ እቃ ህትመት እና አውቶ ማሰልጠኛ ማቴሪያል አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በምዕራብ ጐንደር ዞን የገ/ውሃ ቴ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በምዕራብ ጐንደር ዞን የገ/ውሃ ቴ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ የፅህፈት መሣሪያ ጋርመንት ኮንስትራክሽን ኤሌክትሮኒክስ የግንባታ እቃ ህትመት እና አውቶ ማሰልጠኛ ማቴሪያል አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የፅህፈት መሣሪያ፣

ሎት 2 ጋርመንት ማሰልጠኛ እቃ፣

ሎት 3 ኮንስትራክሽን ማሰልጠኛ እቃ፣

ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ ማሰልጠኛ፣

ሎት 5 የአውቶሞቲቭ ማሰልጠኛ፣

ሎት 6 የግንባታ እቃ፣

ሎት 7 ህትመት

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎችን ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የገብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስዙ ተጫራቾች በመሥሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጂናልና ኮፒ በመለየት ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ የሚወዳደሩበት የግዥውን አይነትና ሎት በመፃፍ በገ/ውሃ ቴክ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 3 ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. የጨረታ ሰነዱ ከገ/ውሃ ቴክ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት እስከ 12 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጨራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀመሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገ/ውሃ ቴክ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 3 በግልፅ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡
  8. ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በገንዳ ውሃ ከተማ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ የዕቃ ማከማቻ ክፍል ድረስ በመምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  11. ተጫራቾች የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን በሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅተን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  12. ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድረግ የለባችሁም፤ በተጨማሪም የእቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  13. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካለ በኮሌጅ የውስጥ ሰሌዳ የምናሳውቅይሆናል።
  14. የአብክመ ግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1/2003 አና በተጨማሪ በቢሮው የሚወጡ የመምሪያ ማሻሻያዎች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡
  15. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  16. ስለጨታው ዝርዝር ኔታ ከፈለጉ በስ.ቁ. 058 33 110 415 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በምዕራብ ጐንደር ዞን የገ/ውሃ ቴ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ

 

Save Tender