Tender Detail

Tender Details

  • Company Ministry of Innovation and Technology (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)
  • Address Lisie G/Mariam, Arada Sub-City, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 09-11-82-52-99
  • Websitehttp://www.mint.gov.et/
  • Deadline01 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Used Items

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አቃቂ በሚገኘው መጋዘን ውስጥ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ያልቻሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ ፕላስቲኮች እና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Ministry of Innovation and Technology (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)


 

የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ ፕላስቲኮች እና ማሽነሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2017

 

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አቃቂ በሚገኘው መጋዘን ውስጥ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ያልቻሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ ፕላስቲኮች እና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ በብረታ ብረት፣ ፕላስቲኮች እና ማሽኖች መልሶ የመጠቀም ፍቃድ እና ከአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የተሰጠውና የቴክኒክ ብቃት ያለው፡፡
  2. በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ መሰረታዊ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ በንክ 1000263705916 ከፍለው ደረሰኝ በማምጣት መውሰድ ይችላሉ፤
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በሚ/ር መሥሪያ ቤቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚ/ር 3ኛ ፎቅ መሰረታዊ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚ/ር 3ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው:: የሚወዳደሩባቸውን ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. መ/ቤቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0913-232 728/0911-907 148 /0973-513 788 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የማያስችል ሁኔታ ከተፈጠረ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ

 

Save Tender