በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር በጣሳ እና ቆርኪ ምርት ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩትን ተረፈ ምርቶች (metal sheets and copper wire scrap) በጨረታ አወዳድሮ ለስድስት ወር የሚቆይ ውል በመግባት ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
ከቆርኪ እና ጣሳ ምርት የሚወጡ ተረፈ ምርቶች
ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር በጣሳ እና ቆርኪ ምርት ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩትን ተረፈ ምርቶች (metal sheets and copper wire scrap) በጨረታ አወዳድሮ ለስድስት ወር የሚቆይ ውል በመግባት ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000050265688 ወይም በዳሽን ባንክ የሂሳብ ቁጥር 0025009238018 ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን ደረሰኝ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የካ አባዶ ኮንደሚንየም መግቢያ በሚገኘው ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ቅጥር ግቢ በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውለታ በመፈጸም ወደ ስራ ካልገባ ያስያዘው ገንዘብ (ሲ.ፒ.አ) ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው አሸናፊነት ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመጥቀስ እና ከሲ.ፒ.ኦ ጋር በማካተት የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ሰነድ በሚገዛበት ቦታ ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ቅጥር ግቢ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሣጥን በዛው ዕለት ከሰዓት በኋላ በ8፡15 ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- በጨረታው ለሚሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲፒኦ በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0970-21-71-57 ወይም 0970-21-72-27 ይጠቀሙ፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ ፡- የካ አባዶ ኮንደሚንየም መግቢያ ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ቅጥር ግቢ
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
