የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 በጀት ዓመት በሆስፒታሉ ፍሳሽ የማስወገድ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 በጀት ዓመት በሆስፒታሉ ፍሳሽ የማስወገድ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለሥራው የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ተፈላጊ ሥራውን መሥራት የሚያስችላቸውን በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የታደሰ ሊብሬ፣ የተመረተበት ጊዜ 1990 ከዚያ በላይና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (በአስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11:30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኃላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በሕዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463299270 ደውሎ መጠየቅ ደችላሉ፡፡
የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
