በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ 2017 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የወጣ የግዥ መለያ ቁጥር የ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጁ የመፀዳጃ ቤቶች በሴፍቲ ታንከር የተጠራቀመውን ቆሻሻ ማስወገጃ መኪና አገልግሎት ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ 2017 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የወጣ የግዥ መለያ ቁጥር የ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጁ የመፀዳጃ ቤቶች በሴፍቲ ታንከር የተጠራቀመውን ቆሻሻ ማስወገጃ መኪና አገልግሎት ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ብርሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ /Website/ ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 10,000.00 (አስር ሺህ) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መኪና አገልግሎት 10,000 (አሥር ሽህ ብር) ሆኖ ጨረታዎች በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም Cpo ወይም የባንክ ጋራንቲ የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በተቋሙ አካውንት 1000053091443 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የውስጥ ገቢ ስም በማስገባት እና እስሊፕ በመያዝ የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ (ይ/ዓለም) ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም ቢሮ ቁጥር 26 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚወጣበት 4/6/2017 ዓ.ም ጨረታው የሚከፈትበት 20/6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.አ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20/6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
2. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም
ስልክ ቁጥር፡- 046 135 0012
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ
