Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ ወደ ሰባተኛ በሚወስደው መንገድ 500 ሜትር ላይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-77-56-09
  • Website
  • Deadline20 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Educational And Training Equipment And Machinery

የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 ዓ/ም ለት/ቤቱ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፤ የፅዳት ዕቃዎችን፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፤ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 ዓ/ም ለት/ቤቱ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፤ የፅዳት ዕቃዎችን፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፤ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመወዳደር የሚችሉት፡-

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
  • የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  • በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ/
  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመከፈል ቢሮ ቁጥር 12 በግንባር በመገኘት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ማስከበሪያ ከሎት 01 እስከ ሎት 05 ላሉት ብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 06 ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች የመሸጫ ዋጋውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች አዘጋጅቶ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ውስጥ በግንባር በመግኘት ማስገባት ይኖርበታል።
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 12 ውስጥ የሚከፈት ሲሆን ከ11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ውስጥ ድረስ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  • ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ለአነስተኛ እና ጥቃቅን መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት በሚፈቀድላቸው ዘርፍ ብቻ እንዲሳተፉ እናበረታታለን፡፡

አድራሻ ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ቤተከርስቲያን አጠገብ ወደ ሰባተኛ በሚወስደው መንገድ 500 ሜትር ላይ ይገኛል፡፡

ስልክ 011-2-77-56-09/10 011-8-68-53-56

አዲስ አበባ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የድላችን

አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender