Tender Detail

Tender Details

  • Company በአያት ቁ.1 አረንጓዴው መንደር የኅብረት ሥራ ማኅበር
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline17 Feb 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በአያት ቁ.1 አረንጓዴው መንደር የህብረት ሥራ ማህበር የ2 ዓመት በጀት ሥራ እንቅስቃሴ ሂሳብ ባለሙያ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

በአያት ቁ.1 አረንጓዴው መንደር የኅብረት ሥራ ማኅበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአያት ቁ.1 አረንጓዴው መንደር የህብረት ሥራ ማህበር የ2 ዓመት በጀት ሥራ እንቅስቃሴ ሂሳብ ባለሙያ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ሂሳብ በውከልና ለማስመርመር ባወጣው ደንብ ቁጥር 171/2016 እና በመመሪያ ቁጥር 5/2013 መጋቢት ወር 2013 ዓ.ም መሰረት ፡-

  1. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል /የምትችል ፣
  2. በሀገሪቱ ሕግ መሰረት የኦዲት ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት/፤
  3. የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሂሳብ ምርመራ በተመለከተ ከፌደራል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ወይም ከሌሎች ህጋዊ አካላት ሥልጠና የወሰደ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፡፡
  4. ተወካይ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪው ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ሂሳብ የመረመረ ቢሆን ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
  5. የህብረት ስራ ማህበራት ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎችን በስራ ላይ ማሰራት የሚችል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚመለከተው ማንኛውንም ኪሳራ እና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን የሚወስድ፡፡
  6. እንደ አስፈላጊነቱ አግባብ ባለው ባለሥልጣን የሚጠየቁ ሌሎች መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  7. 100% ዝርዝር የኦዲት ምርመራ ማድረግ የሚችል፡፡
  8. ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ውል ማስከበሪያ 10% በሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፡፡
  9. ሕጋዊ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ Tin no፣ vat እና ማህተም ያለው/ያላት፤
  10. 2% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል/ የምትችል ተወዳዳሪዎች በአያት ቁ.1 አረንጓዴው መንደር ማህበር ቢሮ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ በፖስታ አሽጋችሁ ከ 3/6/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 10/6/2017 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ጨረታውን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  11. ማኅበሩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  12. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 100 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

 

በአያት ቁ.1 አረንጓዴው መንደር የኅብረት ሥራ ማኅበር

 

Save Tender