Tender Detail

Tender Details

  • Company Agape Saving and Credit Cooperative (አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር)
  • Address ለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ኢምፔሪያል ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 06-56 22 22
  • Website
  • Deadline18 Feb 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በለሚኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ የአጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የስራ እንቅስቃሴ ሂሳብ ባለሙያ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Agape Saving and Credit Cooperative (አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በለሚኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ የአጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የስራ እንቅስቃሴ ሂሳብ ባለሙያ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቶች በአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኤጀንሲ የህብረት ስራ ማህበራትን ሂሳብ በውከልና ለማስመርመር ባወጣው ደንብ ቁጥር 171/2016 እና በመመመሪያ ቁጥር 5/2013 ወር 2013 ዓ.ም መሰረት ፡-

  1. የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. በሃገሪቱ ህግ መሰረት የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  3. የህብረት ስራ ማህበራት ሂሳብ ምርመራ በተመለከተ ከፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ወይም ከሌሎች ህጋዊ አካላት ስልጠና የወሰደ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል።
  4. ተወካይ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪው ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት ህብረት ስራ ማህበራትን ሂሳብ የመረመረ ቢሆን ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
  5. የህብረት ስራ ማህበራት ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎችን በስራ ላይ ማሰማራት የሚችል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ማንኛውም ኪሳራ አስቀድሞ ሃላፊነቱን የሚወስድ፣
  6. እንደ አስፈላጊነቱ አግባብ ባለው ባለስልጣን የሚጠየቁ ሌሎች መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤
  7. 100% ዝርዘር የኦዲት ምርመረ ማድረግ የሚችል፤
  8. ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% በሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፤
  9. ህጋዊ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ TIN NO, VAT እና ማህተም ያላቸው።
  10. 2% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ ተወዳዳሪዎች የአጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበርቢሮ ቁ. 2ኛ ፎቅ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመግዛት ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ ፖስታ በማሸግ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችን ቢገኙም ባይገኙም ታዛቢዎች በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡

 

ማሳሰቢያ ፡- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ በሰአቱ ሳይገኙ ቢቀሩ በተገኙት አባላት ይከፈታል፡፡ ባለመገኘት የሚቀርብ ቅሬታ ተቀባይነት የለውም።

አድራሻ ፡- ለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ኢምፔሪያል ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።

ለበለጠ መረጃ :- 09 06-56 22 22, 09 06-57 22 22

 

 

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

 

Save Tender