Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Textile Share Company (ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር)
  • Address አማራ ክልል ኮምቦልቻ (ወሎ) በዋናው መስሪያ ቤት እና ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5530124
  • Websitehttps://kombolchatextile.com/
  • Deadline03 Mar 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Byproducts

የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አከሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሰረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Kombolcha Textile Share Company (ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 030/2017

 

የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አከሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሰረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. የተለያዩ መጠን ያላቸው የተጠናቀቁ የጨርቅ ተረፈ ምርቶች
  2. የተለያዩ አይነት የጥጥ ቅሪቶችና ተረፈ ምርቶች
  3. የተለያዩ አይነት ብረታ ብረት እና መለዋወጫ ዕቃዎች
  4. የተለያዩ መጠን ያላቸው የተጋቡ የፕላስቲከ ጀሪካኖችና የብረት በርሜሎች እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች በጨረታው ማንኛውም በዘርፉ የታደስ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ  በመክፈል ከአክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይም ከዋናው መ/ቤት/ኮምቦልቻ መግዛት ይችላሉ፡፡

ዕቃዎቹን ዘወትር በስራ ሰዓት ( ከሰኞ-ዓርብ  ከ 2፡00 - 10፡00 እና ቅዳሜ ከ2፡00 -6፡00) ዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ የድርጅቱ መጋዘን ላይ በመመልከት የሚገዙበትን ነጠላ ዋጋ አ/ማህበሩ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በ (CPO) በማስያዝ ከላይ በተገለጹት ቦታዎች ላይ በመገኘት ዋጋ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ጨረታ ማስታወቂያው በተዘጋ በ 3ኛው ቀን ኮምቦልቻ /ወሎ/ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የህዝብ በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡

አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 033-5510627/5510211

(ኮምቦልቻ)

ስልክ ቁጥር 011-5511805 / 5530124

(አዲስ አበባ)

ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ

 

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender