በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በተለያዩ ዞኖች፤ ወረዳዎችና ጤና ኬላዎች በቤተሰብ ደረጃ እየተተገበረ የሚገኘውን የመካከለኛ የምግብ እጥረት በሽታ ህክምና አገልግሎት ለመገምገምና ድጋፍ ለመስጠት ለድጋፋዊ ክትትል አገልግሎት የሚውል /1/ መኪና/ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
Central Ethiopia Regional State Health Bureau (በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በተለያዩ ዞኖች፤ ወረዳዎችና ጤና ኬላዎች በቤተሰብ ደረጃ እየተተገበረ የሚገኘውን የመካከለኛ የምግብ እጥረት በሽታ ህክምና አገልግሎት ለመገምገምና ድጋፍ ለመስጠት ለድጋፋዊ ክትትል አገልግሎት የሚውል /1/ መኪና/ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ፡-
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
በቁጥር |
ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
ምርመራ |
|
1 |
የመኪናው አይነት ሐርድ ቶፕ /ማርክቱ/ የመኪናው ይዘት ፤ ከ2014 ዓ.ም ወዲህ ያለ ሞዴል የመኪና ኪራይ ሁኔታ ፤ የካቲት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 06 ወራት የውል ሁኔታ፤ የመኪና ኪራይና የነዳጅ ወጪን ጨምሮ በFuel log sheet መሰረት የነዳጅ ወጪ በቢሮው በኩል የሚሸፈን ይሆናል። |
1 |
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ይከፈታል። |
በቀረበው ስፔስፍኬሽን መሰረት ዝርዝር መረጃውን በጨረታ ሰነዱ ላይ ይመልከቱ |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በክልሉ ጤና ቢሮ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋና ዶክመንታቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል:: ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በቢሮው ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ውል የሚፈጽም ሲሆን ያሸነፈውን ዕቃ መኪና ክልል ጤና ቢሮ ወራቤ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 046 32 69 229
የማ/ኢትዮጵያ/ክ/መ/ጤና ቢሮ
ወራቤ
