Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት
  • Address ሆሳዕና ከተማ ወደ ወልቂጤ መውጫ መንገድ ካቶሊክ ት/ቤት ጎን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912818102
  • Website
  • Deadline17 Nov 2026, 2:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceበነፃ
  • Bid Securityብር 20,000 (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን በ 9:00 ሰዓት
  • Categories Vehicles Rent

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ለፕሮጀክት መስክ አገልግሎት አነስተኛ መኪኖች ኪራይ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር CDCSE NO 07/2019

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል ሆኖ በየሶስት ወሩ የሚታደስ ውል በመግባት ለፕሮጀክት መስክ አገልግሎት የሚውሉ አነስተኛ መኪኖችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በማዉጣት አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል:: በዚሁ መሰረት ተጫራቾች :-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የመኪና ዓይነት በስሙ የተመዘገበ ወይም ህጋዊ ዉክልና ያለዉ ኦርጂናል ሊብሬ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘረዉን እያንዳንዱን ዋጋ ሞልተዉ / ፈርመዉ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ፋይናንሻል ኦርጂናል ዶክመንት አንድ እና ፍይናሻያል ኮፒ አንድ ቴክኒካል ኦርጂናል አንድ እና ቴክኒካል ኮፒ አንድ ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ኢንቬሎፕ አድርገዉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ እስከ 15ኛዉ ቀን 8:30 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታዉ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛዉ ቀን በቀኑ 8:30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ 9:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: 15ኛዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ዉስጥ አስገብተዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  7. ተጫራቾች የተዘጋጀዉን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ በነፃ ከድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቀርበዉ መግዛት ይችላሉ::
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912818102/0955445261 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ::

የድርጅቱ አድራሻ ሆሳዕና ከተማ ወደ ወልቂጤ መዉጫ መንገድ ካቶሊክ ት/ቤት ጎን ላይ

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት

✨ messages.ai_summary
The Central Ethiopia Design and Construction Supervision Enterprise (Hosanna) seeks to rent small vehicles for project field work under a one-year contract renewed every three months. Bidders need a renewed licence, supplier registration, TIN, VAT and the original vehicle logbook. Open national bid.
Save Tender