Tender Detail

Tender Details

  • Company ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
  • Address ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5-586725
  • Website
  • Deadline13 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየሎቱ ጠቅላላ ዋጋ 1% (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Vehicles Rent

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የዳምፕ ትራክ፣ ሲንግልና ደብል ካፕ መኪናዎችና አውቶቡሶች ኪራይ አገልግሎት

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ


የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር፡ ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/05/2019

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ

የተለያዩ መኪኖች ማለትም 2 ዳም ትራክ መኪና፣ 2 ሲንግል ካፕ መኪና፣ 1 ደብል ካፕ መኪና እና 2 40 ሰው የሚይዝ አውቶቡስ ለ2 ወራት የኪራይ አገልግሎት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ጨረታው ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ.ቁጥር 1000057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡
    አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ፣ ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008, ስልክ ቁጥር 011 5-586725, አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
  7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው።

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
Tana Beles Sugar Factory seeks vehicle rental services for two months: dump trucks, single and double cab pickups, and 40-seat buses. Open to licensed, VAT-registered suppliers on the government supplier list. National open bid.
Save Tender