Tender Detail

Tender Details

  • Company በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 አዲስ ራዕይ ቅድመ መደ/ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ኮከብ ህንፃ አለፍ ብሎ 24 ህንፃ አጠገብ ወይም ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 89 32 560
  • Website
  • Deadline17 Feb 2025, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Educational And Training Equipment And Machinery

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 አዲስ ራዕይ ቅድመ መደ/ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 አዲስ ራዕይ ቅድመ መደ/ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

 የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 002/2017 ዓ.ም

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 አዲስ ራዕይ ቅድመ መደ/ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው::

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር

 የሎት ዝርዝር

 የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ/ በኢትዮጵያ ብር

ሎት-1

 የደንብ ልብስ

 ብር 1000

ሎት-2

 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

 ብር 1000

ሎት-3

 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

 ብር 1000

ሎት-4

 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

 ብር 1000

ሎት-5

 ለፕላንት፤ ማሽነሪ መሳሪያዎች

 ብር 1000

ሎት-6

 ለህንፃ፤ የህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ

 ብር 1000

 

  1. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ሎት የማይመለስ (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 2 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ዋጋው የሚሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ በየሎቱ የተዘጋጀውን የዋጋውን CPO በማካተት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  3. ጨረታው በአስረኛው (በ10ኛው) ቀን ከቀኑ 10፡00 ታሽጎ በ11ኛው /አሰራ አንደኛው/ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጫረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው::ናሙና የማይቀርብባቸው እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው::
  5. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ለትምህርት ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል ::
  6. አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ት/ቤቱ ለጨረታው ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% ድረስ የመቀነስም ሆነ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

አድራሻ ፡- መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ኮከብ ህንፃ አለፍ ብሎ 24 ህንፃ አጠገብ ወይም ጀርባ

ተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር ፡- 011 89 32 560

 

 

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የአዲስ ራዕይ የመጀ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender