Tender Detail

Tender Details

  • Company Tikur Abay Transport PLC (ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማ/)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋዜቦ አደባባይ ስተረሊንግ ህንጻ 3ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-552-7748
  • Websitehttps://tikurabaytl.com/
  • Deadline21 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር ያገለገሉ ትራከር፣ ሲኖትራከር እና ተሳቢዎች እንዲሁም ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Tikur Abay Transport PLC (ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማ/)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር ያገለገሉ ትራከር፣ ሲኖትራከር እና ተሳቢዎች እንዲሁም ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ይህንን ጨረታ እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በሚገኙበት ኮምቦልቻ በሚገኘው የኩባንያው ማሰልጠኛ ተቋም እና አዳማ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት በመሄድ የገዙትን የጨረታ ሠነድ ክፍያ በማሳየት መኪኖችን ማየት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የተሽከርካሪውን ጨረታ መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማስገባት ውድድሩን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  3. ሌላው በሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ላይ በመንተራስ በፐርሰንት አሳንሶ ወይም 8 አስበልጦ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ዘወትር በስራ ሠዓት ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲከስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ በኩባንያው ዋና መ/ቤት መዝገብ ቤት እንዲሁም አዳማ እና ባህር ዳር በኩባንያው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና በመቅረብ የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ኮምቦልቻ እና ባህር ዳር በሚገኘው የኩባንያው ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ መዝጊያው ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በስራ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና በቅርንጫፎች ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ8 /ስምንት ቀናት/ ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ መክፈል ይጠበቅባቸዋል በስምንት ቀን ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ካልቻሉ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም፡፡
  8. ከተሽከርካሪዎች ከስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ወጭዎችን ገዥ ይከፍላል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች መኪናውን የሚረከበው ያሸነፈበትን ገንዘብ ከፍሎ ስሙን ካዞረና ስሙ የዞረ ለመሆኑም የዞረውን ሊብሬ ሲያቀርብ ብቻ ነው::
  10. በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
  11. ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር 011-552-77-48 ወይም 011-557-38-24

 

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር

 

Save Tender