ድርጅታችን ሲነርጂ ፎር ከምዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከ May 28, 2024 ጀምሮ ሂሳቦቻችንን ሕጋዊ ፈቃድ ባላቸው የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድረን ለማስመርመር እንፈልጋለን፡፡
Synergy for Community Development (ሲነርጂ ፎር ከምዩኒቲ ዴቨሎፕመንት)
የውጭ ኦዲት አገልግሎት
ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሲነርጂ ፎር ከምዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን በአደረጃጀትም ረገድ በቦርድ የሚመራ፡ ለትርፍ ያልተመሰረተና በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ደንብ ቁጥር 1113/2019 በምዝገባ ቁጥር 4035 ተመስርቶ በጥቅምት፥ 2012 ዓ.ም ፈቃድ የተሰጠው ሲሆን እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከ May 28, 2024 ጀምሮ ሂሳቦቻችንን ሕጋዊ ፈቃድ ባላቸው የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድረን ለማስመርመር እንፈልጋለን፡፡
በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የውጭ ኦዲተሮችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያለው፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የ ተ.እ.ታ መለያ ቁጥር ያለው፣
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (Tin no) ያለው፣
- ቢያንስ ከሶስት በላይ በሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶችን ኦዲት በማድረግ ልምድ ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ስለድርጅታችሁ የሚገልጽ አጭር መግለጫ/ፕሮፋይል
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት ውስጥ ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃዎቻችሁን እንዲሁም የአገልግሎት ዋጋችሁን በታሸገ ኤንቬሎፕ ከላይ በስም ለተጠቀሰው ድርጅት በሥራ ሰአት በግንባር ቀርበው አልያል P.O Box 2989 እንዲያስገቡ ይጋብዛል፡፡
ማስታወሻ ፡-
- ለአስፈላጊ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913921177/+251 25 411 1346/ ማግኘት ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡-
- ድሬዳዋ ሳቢያን ማድያ ወረድ ብሎ ከመገናኛ ሽሮ በታች ሀሩን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡
ሲነርጂ ፎር ከምዩኒቲ ዴቨሎፕመንት
