በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ አ/ከ/ክ/ከ/ዲ/ግ/ስ/ጽ/ቤት/ም/ቡ/004/2017
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
|
ሎት |
የፕሮጀክት ስም
|
የሚገኝበት ቦታ
|
የጨረታ ዋስትና ብር መጠን |
የተቋራጭ ደረጃ
|
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ
|
|
1 |
ወረዳ 04 አስተዳደር ተጨማሪ ግንባታ ጂ+4 |
ወረዳ 04 |
360,000 |
GC 5 ወይም BC 4 እና ከዛ በላይ |
90 ቀን
|
|
2 |
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሰራተኞች ካፍቴሪያ ግንባታ እና ህንፃ ጥገና |
ወረዳ 5 |
225,000 |
BC 5/ GC 6 እና ከዛ በላይ |
90 ቀን
|
|
3 |
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሰራተኞች ካፍቴሪያ ግንባታ እና ህንፃ ጥገና |
ወረዳ 5 |
225,000
|
BC 5/ GC 6 እና ከዛ በላይ |
90 ቀን
|
|
4 |
ወረዳ 13 ኒኮላ ስፖርት ሜዳ አርቴፊሻል ሳር ማልበስ |
ወረዳ 13 |
100,000
|
GC 7/BC6 እና ከዛ በላይ |
60 ቀን |
|
5 |
ፊሊጶስ ሼድ ቁጥር 1 እና 2 ግንባታ ስራ
|
ወረዳ 11 |
80,000
|
BC 6/ GC 7 እና ከዛ በላይ |
60 ቀን
|
|
6 |
ፊሊጶስ ሼድ ቁጥር 3 እና 4 ግንባታ ስራ
|
ወረዳ 11 |
80,000
|
BC 6/ GC 7 እና ከዛ በላይ |
60 ቀን
|
|
7 |
ፊሊጶስ ሼድ ቁጥር 31/A እና 31/B ግንባታ ስራ
|
ወረዳ 11 |
80,000
|
BC 6/ GC 7 እና ከዛ በላይ |
60 ቀን
|
|
8 |
ፊሊጶስ ሼድ ቁጥር 30 እና 32 ግንባታ ስራ
|
ወረዳ 11 |
80,000
|
BC 6/ GC 7 እና ከዛ በላይ |
60 ቀን
|
|
9 |
ፊሊጶስ ሼድ ቁጥር 33 እና 42 ግንባታ ስራ
|
ወረዳ 11 |
80,000
|
BC 6/ GC 7 እና ከዛ በላይ |
60 ቀን
|
|
10 |
ወረዳ 9 ወጣት ማዕከል እድሳት ስራ (በድጋሚ የወጣ ጨረታ) |
ወረዳ 09 |
90,000
|
BC 7/ GC 7 እና ከዛ በላይ |
60 ቀን
|
- ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር (የ2017 ዓ.ም) የከፈሉ፤ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፤ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል። በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፤ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሃያ አንድ (21) ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በምህንድስና ግዥ ቡድን 2ተኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 202 በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዘው በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው (ሃያ ሁለት) የመቁጠሪያ ቀን (Calendar Days) ጠዋት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዥ ቡድን 2ተኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 202 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 22ኛው የስራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ (unbalanced Bid) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
- ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
- በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያ በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡-
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በመረጠው አንድ ሎት ብቻ ይሆናል። ከአንድ ሎት በላይ ተወዳድሮ የተገኘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ በግራ በኩል ቢሮ ቁጥር 202 በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።
- አድራሻ፡- መድሃኒአለም መሰናዶ ት/ቤት አካባቢ ራስ ኃይሉ ስፖርት ማዕከል ጎን በሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ መሆኑን እንገልጻለን።
- ስልክ ቁጥር ፡- 011-8-27-93-24
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
