Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን
  • Address ባህርዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 058 32 08 656
  • Website
  • Deadline04 Mar 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Supplies And Services

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ነባር የመረጃ ማዕከል የማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING) ሥራ ማለትም፤ ሎት 1 - ነባር መረጃ ማዕከል የማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING)፣ ማዕከሉን ለማሳደግ የሚውሉ እቃዎችን የማቅረብ፣ የኢንስታሌሽን፣ ማይግሬሽንና ኮንፊግሬሽን ስራዎችን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ በካፒታል በጀት ማሰራት ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን


 

ግልፅ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

 

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ነባር የመረጃ ማዕከል የማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING) ሥራ ማለትም፤

  • ሎት 1 - ነባር መረጃ ማዕከል የማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING)፣ ማዕከሉን ለማሳደግ የሚውሉ እቃዎችን የማቅረብ፣ የኢንስታሌሽን፣ ማይግሬሽንና ኮንፊግሬሽን ስራዎችን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ በካፒታል በጀት ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የሚወዳደሩበት ግዥ ጥቅል ዋጋ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (AT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የተጠየቁ እቃዎችን በማቅረብ የኢንስታሌሽን፣ ኮንፊግሬሽንና ማይግሬሽን ሥራዎችን መሥራት እና ሙያዊ ሥልጠናዎችን መስጠት የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የሚሠሩ የመረጃ ማዕከል ማሳደግና ማዘመን (ኢንስታሌሽን፣ ኮንፊግሬሽንና ማይግሬሽን ሥራዎችን ጨምሮ) እና የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 20 በመምጣት
  8. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዳታ ማዕከል ማዘመንና ማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING) ሥራ እና የዕቃዎችን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የቴከኒካል ሰነዳቸውን፣ የንግድ ፈቃድ ሰነድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሻል (የዋጋ) ሰነዳቸውንና የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ሰነድ በሌላ ፖስታ ለየብቻ በታሸጉ ሁለት ፖስታዎች በማድረግ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በ30ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል።
  12. አሸናፊው የሚለየው በሎት (ምድብ) ይሆናል።
  13. ተጫራቾች በቴከኒካል ሰነዳቸውም ሆነ በፋይናንሻል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ማህተም ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 32 08 656 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን

ባህርዳር

 

Save Tender