የሀድያ ልማት ማህበር (ሀልማ) የ2016 በጀት ዓመት የማኅበሩን ሂሳብ በታወቀ የኦዲት ሥራ ድርጅት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
Hadiya Development Assocation (የሀድያ ልማት ማህበር (ሀልማ))
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ልማት ማህበር (ሀልማ) የ2016 በጀት ዓመት የማኅበሩን ሂሳብ በታወቀ የኦዲት ሥራ ድርጅት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የታደሰ የኦዲት ፈቃድ ያለው፣ የዓመቱን ግብር የከፈለ፤ በኦዲት ሥራ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ተገቢ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሆሳዕና በሚገኘው ዋና ጽ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን የማይሆን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ የልማት ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0996-70-23-54፤ 071 463 5368፣ 0923 683 5395
ዋና ጽ/ቤቱ - ሆሳዕና
የሀድያ ልማት ማህበር (ሀልማ)
