በቤ/ጉ/ክ/መንግስት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ በከተማ አስተዳደሩ ስር ላሉ ትጉ ሠራተኞችና ለስፖርት መምህራን አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ በመደበኛ በጀት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡
በቤ/ጉ/ክ/መ/የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 001/2017
በቤ/ጉ/ክ/መንግስት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ በከተማ አስተዳደሩ ስር ላሉ ትጉ ሠራተኞችና ለስፖርት መምህራን አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ በመደበኛ በጀት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡
- ሎት አንድ የደንብ ልብስ
- ሎት ሁለት- የስፖርት ትጥቅ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ።
1ኛ/ ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የስራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2ኛ/ ተጨማሪ የእሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል::
3ኛ/ ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
4ኛ/ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት(ቲን ነምበር)
5ኛ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር ማስያዝና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የማንኛውንም የባንክ ቢድ ቦንድ የማንቀበል መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን።
6ኛ/ ተጫራቾች የእቃውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ በቤ/ጉ/ክ/መንግስት በአሶሳ ከተማ አስ/ር ገ/ኢ/ል መምሪያ ግዥና ንብረት አስ/ር ደ/የስራ ሂዳት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 200 /ሁለት መቶ ብር / ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ::
7ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ሞልተው በየሎቱ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ፣ ሁለት የቴከኒካል ኮፒ ዶክመንት እና አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክመንት ፋይናንሻል ኮፒ ዶክመንት ለእያንዳዳቸው በተለያየ ፖስታ በማድረግ በአንድ ማዘር ፖስታ በታሸገ እና ሁለት ኤንቨሎፕ ታሽጎ ሰነዱን በገዙበት ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ/አለባቸው።
8ኛ ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9ኛ/ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል::
10ኛ/ አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በነጠላ ዋጋ ሆኖ የተሻለ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበና የተሻለ ናሙና ያቀረቡ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
11ኛ/ መምሪያው የተሻለ ዘዴና አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12ኛ/ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ለእያንዳንዱ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 057 258 388 /091 718 1578/091 742 6395/091 085 08456 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በቤ/ጉ/ክ/መ/የአሶሳ ከተማ አስተዳደር
ገ/ኢ/ል/መምሪያ
