በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፑል ፋይናንስ ጽ/ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አውጥቶ የተለያዩ የቢሮ አገልግሎቶችና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለ2ኛ ዙር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ለሚ ኩራ ክ/ከ/ስ/አ/ፑ/ፋ/ጽ/ቤት 002/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፑል ፋይናንስ ጽ/ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አውጥቶ የተለያዩ የቢሮ አገልግሎቶችና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለ2ኛ ዙር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፡-
- ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና
ሎት-01 የቢሮ እቃዎች ግዥ ብር 1000
ሎት-02 የፈርኒቸር ጥገና ብር 2,000
ሎት-03 የመኪና ጌጣጌጥ ግዥ ብር 2,000
ሎት 04 የደንብ ልብስ ብር 5,000
ሎት 05 የመኪና ጎማ ብር 10,000
ሎት 06 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ብር 20,000
ሎት-07 የኤሌክትሮኒክስ ሃርድ ዌር ጥገና ብር 3,000
ሎት-08 የጽዳት እቃዎች ግዥ ብር 3,000
በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ወይም የባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ድረስ ሰነዱን የማይመለስ ለየአንዳንዱ ሎት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ሀያት አደባባይ ኢንጆይ ሞል 3ኛ ፎቅ ሥራ አስኪያጅ ፑል ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ. 306 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሂሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ (Finance and technical documents) ዋናና ቅጅ (original and copy) እያንዳንዱ ሎት ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በክ/ከተማው ስ/አ/ፑል/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 306 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታው በወጣ 11 የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደርያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በክ/ከተማው ግዥ ቡድን በአካል ቀርበው ውል መግባት አለባቸው።
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በክ/ከተማው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልጻለን፡፡
- በጨረታ ተሳታፊ የሆኑ ድርጅቶች የሚወዳደሩበትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ 3 ቀን ቀድመው ለጽ/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው። አማራጭ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- አድራሻ ሃያት አደባባይ ወደ ጎሮ መስመር 500 ሜትር ገባ ብሎ ኢንጆይ ሞል ላይ እንገኛለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን እቃ አስከ የመ/ቤቱ መጋዘን ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች ግዥ ቡድን ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ስልክ:- 09 41 102 720/09 37 767 155
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት
