በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክከ በወረዳ 08 ውስጥ የሚገኘው ሙሴ አንደኛ ደረጃትቤት ለ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በወረዳ 08 ሙሴ አንደኛ ደረጃ/ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙት/ 002/2017 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክከ በወረዳ 08 ውስጥ የሚገኘው ሙሴ አንደኛ ደረጃትቤት ለ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
- ቋሚ እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣
- አላቂ የህክምና ዕቃ የተለያዩ ጥገና ስራዎች እና ህትመት፤
ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ እና በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
- የቲን ሰርተፊኬት TIN እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢው አካል የተሰጠ ማረጋጋጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 150/ አንድ መቶ ሃምሳ ብር በመክፈል ከት/ቤቱ ገንዘብ ቤት መውሰድ ይችላሉ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000(አራት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት 7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ባሉት 3 የስራ ቀናት ውስጥ ከት/ ቤቱ ጋር ውል በመዋዋል በ5 ቀናት ውስጥ እቃውን በራሱ ወጭ በራሱ መኪና አጓጉዞ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የገዛችሁትን የጨረታ ሰነድ ምንም ሳይቀነስ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ በሁለት ኤንቨሎፕ ታሽጎ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፤ በመጨረሻው 10ኛው ቀን በ11:30 ሰዓትየጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ድርጅት የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10/100/ አስር በመቶ ያሸነፈበትን እቃ ዋጋ በ CPO በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር ውል ይፈርማል።
- ት.ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ከንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወደ ሃኪም ማሞ ቤት በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ፤ ስልክ ቁጥር 0114 424694 /0114 70 7199
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
በወረዳ 08 ሙሴ አንደኛ ደረጃ/ት/ቤት
