የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለ2017 የበጀት አመት ለ2ኛ ግዜ የምግብና መኝታ አገልግሎት የሚውሉ ህጋዊ ተጫራቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Adama City Football Club (የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለ2017 የበጀት አመት ለ2ኛ ግዜ የምግብና መኝታ አገልግሎት የሚውሉ ህጋዊ ተጫራቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ተጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተወዳዳሪዎች ሟሟላት ያለባቸው መስፈርቶች /የተጫረቶች መመሪያ/:-
-
- ማንኛውም ድርጅት /ግለሰብ እና በዘርፉ የተሰማሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍታድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
-
- ተጫራቶች ቫት ተመዝጋቢ እና የተጨማሪ እሰቴ ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል አዳማ ከተማ መዘጋጃ ቤት ሲንቄ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1054551161211 በማስገባት ጨረታው ከወጣባት የስራ ቀን ጀምሮ አዳማ ከተማ እግር ኳስ ጽ/ቤት መግዛት ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለምግብና መኝታ አቅርቦት 50,000.00 /ሃምሳ ሺ/ ብር በባንክ ቼክ የተረጋገጠ ሲፕኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን የሚቆይ ሆኖ በ 11ኛው የስራ ቀን በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም ሆኖም 11ኛው ቀን በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናሻልን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒውን እና ኦርጅናሉን በተናጠል በማቅረብ አዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤትበመቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን ማስገባት ይችላሉ።
- የምግብ ዝግጀት ለስፖርታኛ ምግብ በሚዘጋጅበት አደራሽ ውስጥ ከአልኮል መጠጥ፣ ከተለያዩ ሱስ አስያዥ፣ ዕፆች፣ ጭፈራ ቤት እንዲሁም ስፖርታኛን ሊረብሹ የሚችሉ የፋብሪካ ድምፅ የራቀ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በቂ የማድቤት እና የምግብ ቁሳቁስ ከበቂ የሰው ሃይል ጋር ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች በ2016 ዓ.ም በዚህ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ መሆኑን የሚገልፅ የስራ ልምድ ከንግድ እና ገበያ አገልግሎት ፅ/ቤት እና ሲሰሩ ከነበረበት ቦታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
