Tender Detail

Tender Details

  • Company የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address በተለምዶ አበቤ ሱቅ ፊት ለፊት ያለውን አስፋልት ተሻግሮ እንግሊዝ ኤምባሲ ጎን ባለው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-68-60-87
  • Website
  • Deadline07 Feb 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Supplies And Services

የካ ቅደመ 1ኛ ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የካ ቅደመ 1ኛ ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የግዢ መለያ ቁጥር 002/2017

ሎት 1/ የሠራተኛ ደንብ ልብስ

ሎት 2/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

ሎት 3/ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

ሎት 4/ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች

ከላይ ዝርዝራቸው የተጠቀሱትን ዕቃዎችን ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  • በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
  • የዘመኑን ግብር የከፈለ
  • የቫት ከፋይ ሆነ
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና የቲን ቁጥር የሚያቀርብ
  • ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ከጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ተጫራቾች የግዢ ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በየሎቱ የበጀቱ 0.5 /% ወይም ሎት 1 /ብር 4000 /አራት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት2 /2,600/ ሁለት ሺ ስድስት መቶ ብር /ሎት 3 2,100 /ሁለት ሺህ አንድ መቶ ብር ብቻ/ ሎት 4  /4,300/ አራት ሺህ ሦስት መቶ/ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒአ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ /ቢድቦንድ /10% በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ አሥረኛው የሥራ ቀን ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ እንዲሁም ከተጠየቀው እስፔስፊኬሽን ውጪ ዕቃ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳዳሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው::
  • በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  • ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አድራሻ፡- በተለምዶ አበቤ ሱቅ ፊት ለፊት ያለውን አስፓልት ተሻግሮ እንግሊዝ ኤምባሲ ጎን ባለው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ
  • ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116-68-60-87/0911-83-22-42/0932-89-86-96 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ማሳሰቢያ ፡- ዋጋው የሚሞላው በወሰዳችሁት የጨረታ ሰነድ ላይ ነው፡፡

 

የካ ቅድመ 1ኛ ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender