Tender Detail

Tender Details


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል በዩኒሴፍ በጀት ከዚህ በታች በሎት በቀረበው ዝርዝር መሰረት ግዥ ለመከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 10/2017

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል በዩኒሴፍ በጀት ከዚህ በታች በሎት በቀረበው ዝርዝር መሰረት ግዥ ለመከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም -

ሎት 1 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች የአካል ድጋፍ ቁሳቁስና የትምህርት መረጃ መሳሪዎች

ሎት 2 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች የሞንቶሶሪ የትምህርት መረጃ መሳሪዎች ኪት ግዥ

ሎት 3. የሞንቶሶሪ ሸልፍ የቢሮ ወንበር ግዥ

ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ ግዥ

ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ ፡-

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፤ የተጫራቾች የአቅሪቢነት ምዝገባ
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 1፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 - 6:00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ / በሲፒኦ ወይም አንኮንድሻናል ባንክ ጋራንቲ ብቻ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
  6. ተጫራቶች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በ2 ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየ ብቻ በማድርግ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ውስጥ በማሽግ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይቻላል። አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000,00 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046212-43-02/03

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ሀዋሳ

 

 

Save Tender