Tender Detail

Tender Details

  • Deadline03 Feb 2025, 9:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Home Appliance And Supplies

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ሞተርሳይክሎች፣ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 17/2017

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ሞተርሳይክሎች፣ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቀበት በቅርብ ጊዜ የተሰጠው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  2. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00- 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በጉምሩከ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫንፍ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቶች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም በታዛቢ ፊት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።
  6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 4:00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
  7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ቢቀር የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለጸ በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት C.P.O ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender