በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
DEBRE MARKOS COLLEGE OF TEACHER EDUCATION (ደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ሎት 1 የኒሳን ገልባጭ የመኪና እቃ 5. ሎት 5 የህንፃ መሳሪያ
2. ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ 6. ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
3. ሎት 3 የላብራቶሪ እቃዎች 7. ሎት 7 የጽዳት እቃዎች
4. ሎት 4 የስፖርት እቃዎች
ስለሆነም ተጫራቾች፣
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ ቲን ሠርተፊኬት እና የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ሠርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በደ/ማ/መም/ትም/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 04 ብር 200 የማይመለስ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር /Specification /ከጨረታ ሠነዱ ጋር ተያይዟል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ፖስታውን በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በስራ (ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ኮሌጁ 2% ዊዝሆልዲንግ እና 7.5% ቫት ይሰበስባል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም ፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ እንደ አስፈላጊነቱ በሎት ወይም በተናጠል ይሆናል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587712914 ወይም 0587715974
ደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
