የመዝናኛ ክበባትን ኦዲት ለማድረግ በወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የአዲሱ ገበያ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር በስሩ ለሚያስተዳድራቸውን አራት መዝናኛ ከበባት የ2016 ዓ.ም የአንድ አመት የሂሳብ ስራዎችን የሚያሳይ አዲት የግልፅ ጨረታ በማውጣት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
አዲሱ ገበያ ሸማቾች ኃ/የተወሰነ የሕብረት ሥራ ማህበር
ግልጽ የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
የመዝናኛ ክበባትን ኦዲት ለማድረግ በወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የአዲሱ ገበያ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር በስሩ ለሚያስተዳድራቸውን አራት መዝናኛ ከበባት የ2016 ዓ.ም የአንድ አመት የሂሳብ ስራዎችን የሚያሳይ አዲት የግልፅ ጨረታ በማውጣት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በኦዲተርነት የሙያ መስከ መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትወዳደሩ በግልፅ ጨረታ የጋበዝን መሆናችንን እየገለፅን ለመወዳደር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም፤
- በዘመኑ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው፣
- የታደሰ የስራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ፣
- ከዚህ በፊት በአዲት ሙያ ተሰማርቶ የነበረ እና የስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- በኢትዮጵያ ኦዲት ቦርድ በኦንላይን ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የሚጫረቱበትን 2% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፣
- ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10% CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት የሚችሉ እና የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ በሚያቀርበው የውል ሰነድ ህጋዊ የውል ስምምነት መዋዋል የሚችሉ ሆነው ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 4 በመግዛት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የአዲቱ ስራ እንደ ተጠናቀቀ ሪፖርቱን ለጉ/ክ/ከተማ ህብረት ስራ ኦዲት ቡድን አቅርቦ ካስተቸ /ካስገመገመ/ በኋላ ለአመራር ቦርዱ የሚያቀርብና ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ማፀደቅ የሚችል መሆን አለበት፤
ማሳሰቢያ ፡- ማህበሩ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት፤ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-111-54-60-41 ይደውሉ፡፡
አዲሱ ገበያ ሸማቾች ኃ/የተወሰነ የሕብረት ሥራ ማህበር
