Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉ/ክ/ከ/አዲስ ተስፋ የመጀ/ደረጃ እና የካቲት 12 ቅ/መ/ደ/ት/ቤት
  • Address ሽሮ ሜዳ 31 ቁጥር አቶቢስ ማዞሪያ ወደ ኪዳነምረት መሄጃ መንገድ አዲስ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ኪዳነምረት ታክሲ መያዥው 50 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111-54-55-13
  • Website
  • Deadline04 Feb 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Maintenance And Repair

በጉ/ክ/ከ/አዲስ ተስፋ የመጀ/ደረጃ እና የካቲት 12 ቅ/መ/ደ/ት/ቤት የ2017 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በውስጥ ገቢ ሁለተኛ ዙር አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች የጥናት ስራዎች በሎት ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በጉ/ክ/ከ/አዲስ ተስፋ የመጀ/ደረጃ እና የካቲት 12 ቅ/መ/ደ/ት/ቤት


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2017

 

በጉ/ክ/ከ/አዲስ ተስፋ የመጀ/ደረጃ እና የካቲት 12 ቅ/መ/ደ/ት/ቤት የ2017 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በውስጥ ገቢ ሁለተኛ ዙር አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች የጥናት ስራዎች በሎት ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም

የጨረታ ማስከበሪያ ፡-

ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃ 4,000                    ሎት 3 የተለያዩ አድሳትና ጥገና 3,000

ሎት 2 አላቂ የትምህርት እቃ 1,000              ሎት 4 ማሽነሪ ጥገና 4,000

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ደርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. የሚወዳደሩበትን በንግድ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ዕቃ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሽሮሜዳ በሚገኘው አዲስ ተስፋ የመጀ/ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 በመምጣት ወይም ወኪሎቻችሁን በመላክ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. የእቃዎች ዋጋ 15 ፐርሰንት ቫት ተጨምሮ ይቅረብ። ባይቀርብ እንደተጨመረ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ መሙላት አለባችሁ።
  5. የምታስገቧቸው ሰነድ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም። ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነዱ ውድቅ ይሆናል።
  6. ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ ጥቃቅንና አነስተኛ እቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በትምህርት ቤቱ ስም የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ያላቀረበ ተጫራቾች መወዳደር አይችልም።
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን በቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት ይችላሉ።
  9. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ በ10ኛው ቀን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በተገኘው ሰው ቢሮ ቁጥር-2 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን በዓል ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  10. የጨረታው የፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ ላይ የተጫራች ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. አሸናፊ ሆኖው የተመረጡ ድርጅቶች በራሳቸው ትራንስፖርት ወጪ ት/ቤት ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
  12. እንደ አስፈላጊነቱ ት/ቤቱ 20% የመጨመር 25% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ሽሮ ሜዳ 31 ቁጥር አቶቢስ ማዞሪያ ወደ ኪዳነምረት መሄጃ መንገድ አዲስ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ኪዳነምረት ታክሲ መያዥው 50 ሜትር ገባ ብሎ

 

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0111-54-55-13/0111-54-34-66

 

በጉ/ክ/ከ/አዲስ ተስፋ የመጀ/ደረጃ እና የካቲት12 ቅ/መ/ደ/ት

 

Save Tender