በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለመንግስት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለመንግስት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1ኛ. ሞተር ባለሁለት ጎማ TVS 125cc
2ኛ. ወንበር ሃይ ባክ መንሽን
3ኛ. ጠረጴዛ
4ኛ. ላፕቶፕ ኮር አይ 3 (Laptop i5)
5ኛ. ኮምፒውተር ዴስክቶፕ Dell እና
6ኛ. የመኪና ጎማ 7.5 OR 16 LT 8TR/DUN LOP/ በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች ቀርባችሁ እንድትወዳደሩ እንገልፃለን፡፡
በዚሁ መሠረት ፡-
- ለጨረታ የሚወዳደሩ የንግድ ፊቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ማቅረብ የሚችሉ እና እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.ዕ.ታ (VAT)ን የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክሜንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ27 (ሃያ ሰባት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመጻፍ ፊርማው ማቅረብ አለባቸው።
- ለጨረታ የሚወዳደሩ የሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ዋናና ቅጂ (copy) በሰም አሽገው ኤንቨሎፕ በማቅረብ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጨረታ ወደ ተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ከጨረታ ተወዳዳሪዎች ውስጥ ለጨረታ አሸናፊ የሚሆን ሰው ለፍ/ቤቱ የቢሮን ዕቃ በጊዜ ማስረከብ (መስጠት) አለበት፡፡
- ለጨረታ የሚቀርብ ጨረታ ላይ በተገለጸው specification መሠረት ማቅረብ አለበት።
- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ሲያገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
