የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት ለደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት1- የተዘጋጁ ልብሶች እና ሎት2- ጫማ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ማ/ዮ/ብ/ግ/ጨ/23/2017
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት ለደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብሶች ማለትም-
- ሎት1- የተዘጋጁ ልብሶች
- ሎት2- ጫማ
በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት (የታክስ ክሊራንስ) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ማለትም ለሎት1-የተዘጋጁ ልብሶች 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለሎት- 2-ጫማ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችሉ
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ወይንም አዲስ አበባ 4 ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 ከሚገኘው ቢሯችን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ብር ሶስት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታውን ፋይናንሻል ዶክመንት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቀለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 771 66 91/058/178 00 37/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
