በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሁለተኛው ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-002/2017
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ግዢ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት :-
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን አግባብ ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ከግዥ ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት በኦን ላይን የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢመሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት ቀደም ብለው ናሙና የሚያስፈልጋቸው እቃዎችን እንዲሁም የፎቶ ናሙና የሚያፈልጋቸዉ እቃዎች በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚቻል ሲሆን ለሎት /1/ የአላቂ የቢሮ እቃዎች 15,000 / አስራ አምስት ሺህ ብር/፤ ለሎት /2/ የደንብ ልብስ 10,000 /አስር ሺህ ብር/፤ ለሎት /3/ የጽዳት እቃዎች 15,000 |አስራ አምስት ሺህ ብር/፤ ለሎት /4/ ቋሚ እቃዎች 7,500 /ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/፤ ለሎት /5/ የቋሚ አላቂ እቃዎች 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/፤ ለሎት /6/ የአገልግሎት ግዥ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሲሆን ለሁሉም ሎቶች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሲፒኦ ውጭ ሌላ የጨረታ ማስከበሪያ አንቀበልም፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት ውስጥ የተዘረዘሩ እቃዎችን ዋጋ ሲሞሉ ከቫት በፊትና ከቫት ጋር እያንዳንዱን እቃ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ መጠየቂያ ረድፍ በግልጽ ስረዝ ድልዝ ሳይኖር ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ በመጠቀም የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሌላ ቅጽ የሚጠቀሙ ተጫራቾች ጨረታ ውስጥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውንመ አድራሻቸውን፣ የድርጅቱን ሙሉ ስም በየአንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ሰነዶችን በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፤ ለወደፊቱም የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፤ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማስል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠየቁትን ማስረጃዎች አሟልተው፣ አሽገው አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአስረኛው የስራ ቀን 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ አካል ማሸነፉ እንደተገለፀበት ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሱ እቃዎች ዝርዝር በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የእቃ አይነት ለአንድ እቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በአንድ እቃ አይነት ሁለት ሳምፕል ያቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
አድራሻ፡- ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ብሩክ ክሊኒክ 200 ሜትር ገባ ብሎ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08
አስተዳደር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቅጥር 6ሀ
ለበለጠ መረጃ ስለክ ቁጥር፡- 011-8-32-96-62
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት
