በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የተለያዩ ግዢዎችን መሳሪያዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።
በልደታ ክ/ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የተለያዩ ግዢዎችን መሳሪያዎችን ለመግዛት የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ፡፡
ሎት- 1 ቋሚ እቃ ፈርኒቸር——2500.00 ብር
ሎት- 2 ቋሚ እቃ ኤሌክትሮኒክስ ---- 10,000.00 ብር
ሎት -3 የደንብ ልብስ የልብስ ስፌት ---3000.00 ብር
ሎት 4 የፅዳት እቃ ----2000.00 ብር
ሎት- 5 ህትመት----- 1000.00 ብር
ሎት -6 መዳኒትና የህክምና እቃዎች ሪኤጀንት ---- 3000.00 ብር
ሎት -7 የቢሮ አድሳትና ግንባታ—6000.00 ብር
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ሎቶችን ብቃት ያላቸው እና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ መ/ቤቱ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዚህ መሰረት ፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፡ቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑ ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/አስ/ኤጀንሲ ድህረ- ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር የጨረታውን አጠቃላይ ድምር 0.5% በማስያዝ በተለየ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ በየሎት ብር 100 በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን 1 ኦርጂናል እና 1 ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናቶች በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ቢሮ 310 ለጨረታው 03
- የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ የስራ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በተጨማሪም መ/ቤቱ ባዘጋጀው ኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የፍላጎት መማለጫ ላይ ዋጋው በትክክል ካለ ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ እንዲሞላ በማድረግ ተጫራቾች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር በመደመር ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- ኮምፒተር የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ኮምፒውተር ሳምፕል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ መከፈቻ ላይ የዘገየ ተጫራች በውድድሩ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈጻሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የመ/ቤቱ ቁጥር 0115 150 015/0115 150 083
አድራሻችን ፡- ከፍተኛ ፍ/ቤት በሄለን ህንጻ በሚወስደው አስፋልት በቤኬር ህንፃ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ
በልደታ ክ/ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ
