የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ መስጫ ኪት (First Aid Kit) ብዛት 1500 በሚሸጠው ሰነድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር
የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ መስጫ ኪት (First Aid Kit) ብዛት 1500 በሚሸጠው ሰነድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን::
- ህጋዊ የታደሰ የስራ ፈቃድ፣ ግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፤
- የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በተቋማችን ኢሜል አድራሻ ERCS-TI@redcrosseth.org ወይም ቴሌግራም አድራሻ @redcrosstrainingeth ያግኙን ወይም በግንባር በመገኘት በሳጥኑ ውስጥ የሚካተቱን እና የሳጥኑን ልኬትና አይነት የያዘ ዶክመንት በብር 400.00 በመግዛት ዋጋ መስጠት፤
- በጨረታው ለመወዳደር ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል፤
- የጨረታ ሰነዱን በፖስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በግንባር ቀርቦ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት እሁድን ሳይጨምር ዘወትር በስራ ሰዓት ሳሪስ አደይ አበባ ገባ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማነበር የሰብዓዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ማስገባት ይኖርባችኋል፤
- ሳምፕል ማያያዝ ይኖርባችኋል፤
- የምታቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለጽ ይኖርባችኋል፤
- ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አለማሟላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፤
- ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ
የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማኀበር ማሰልጠኛ ተቋም
ሳሪስ ከአደይ አበባ 400 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ 0114420235
አዲስ አበባ
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Red Cross Society's Humanitarian Services Capacity Building Center seeks to buy 1,500 First Aid Kits via open tender. Bidders must submit a valid renewed business license, tax payer certificate and other documents, plus a sample; prices must include VAT.
