Tender Detail

Tender Details

  • Company መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address ኮተቤ መሳለሚያ ሳራ መናፈሻ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-22-52-99-97
  • Website
  • Deadline29 Jan 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም በመ/ቁ 5561 ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ሲሆን የመስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት የ2024 እ.ኤ.አ የስራ ዘመን የሂሳብ እንቅስቃሴው በሙሉ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።

መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም በመ/ቁ 5561 ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ሲሆን የመስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት የ2024 እ.ኤ.አ የስራ ዘመን የሂሳብ እንቅስቃሴው በሙሉ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው፤
  • የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ስራውን ሙያው በሚጠይቀው ስታንዳርድ እና ጥራት በወር ጊዜ ውስጥ ሰርተው የሚያጠናቅቁ፤
  • ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ ፤

  • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ በመገኘት የስራውን ስፋትና የዶክመንት ብዛት በማየት የስራውን ዋጋ በሰም በታሽገ ፖስታ በድርጅቱ ቢሮ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
  • ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ስሙን፣ አድራሻውንና ማህተሙን በግልጽ ማድረግ ይኖርበታል፤ ከተጠቀሰው ጊዜ ውጭ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ኮተቤ መሳለሚያ ሳራ መናፈሻ አጠገብ መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት

ስልክ ፡- 09-22-52-99-97/09-45-22-22-24

 

መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅት

 

Save Tender