የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ለአገልግሎት የሚጠቀማቸውን ኤሌክትሮኒክስ ማለትም የሞባይል ቀፎ እና ላፕቶፕ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ለአገልግሎት የሚጠቀማቸውን ኤሌክትሮኒክስ ማለትም የሞባይል ቀፎ እና ላፕቶፕ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት -
- ከላይ በተጠቀሱት ዘርፍ ሥራዎች የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ በፋይናንስ መሥሪያ ቤቶች ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማንኛውም ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ሙሉ መረጃ የያዘን ሰነድ ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/ አስ/ዳ ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ CPO ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው፣ ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ እስከ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብና ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታውን አስመልከቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 046807970 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የርዕሰ
መስተዳድር ጽ/ቤት
