ትውልድ አድን ተግባር ልማት ድርጅት አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እ.ኤ.አ ከጥር 1 ቀን 2024 ዓ.ም እስከ 31/2024 ዓ.ም የሂሳብ ሪፖርቱን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል።
ትውልድ አድን ተግባር የልማት ድርጅት
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ትውልድ አድን ተግባር ልማት ድርጅት አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እ.ኤ.አ ከጥር 1 ቀን 2024 ዓ.ም እስከ 31/2024 ዓ.ም የሂሳብ ሪፖርቱን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከታች በተቀመጠው አድራሻ ማስረጃቸውን በማቅረብ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የሙያ ማረጋገጫ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማስረጃ የሚያቀርብ፣
- ከኢትዮዽያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ፈቃድ ያለው እና
- መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሂሳብ በመመርመር ልምድ ያለው ተወዳዳሪዎች ለሥራው የሚያስከፈሉትን ዋጋ እና ሠርተው የሚያስረከቡበትን ጊዜ የሚጠቅሱ ተጫራቾች አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ከታች ባለው ስልክ ቁጥር መደወል ይችላሉ::
አድራሻ ፡-
አዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ገደራ አካባቢ ገዛኸኝ ህንፃ አጠገብ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በሚገኘው የድርጅት ጽ/ቤት የምንገኝ ሲሆን ፤
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0912848425 ማግኘት ትችላላችሁ::
ትውልድ አድን ተግባር የልማት ድርጅት
