Tender Detail

Tender Details

  • Company በደሴ ከተማ አስ/ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ
  • Address ደሴ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0331118629
  • Website
  • Deadline06 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electrical And Electromechanical

በአማራ ብ/ክ/መንግስት የደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ ለደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክሶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በደሴ ከተማ አስ/ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር-004/2017

 

በአማራ ብ/ክ/መንግስት የደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ ለደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክሶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ /ሰፕላይ ሊስት/ ላይ የተመዘገቡ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በስራ ሠዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋውን 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የሚፈለጉትን ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ከማስገባቱ በፊት ናሙና አቅርቦ መረጋገጥ አለበት፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2017 ዓ/ም 4:00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ የሥራ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ይዘው በቀረቡበት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2017 ዓ/ም 4:00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4:30 ሠዓት ደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል።
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 የተጠቀሰው ቢኖርም ተጫራቾች በአካል ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት እያግደውም፡፡
  11. ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሆኖ ለመለየት አሻሚ ነገር መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለም ስለመሰረዙ ሰነዱን የሞላው አካል ፊርማውን ማስቀመጥ አለበት፡፡
  12. አሸናፊው አቅራቢ የሚለየው በተጠየቁት ጠቅላላ እቃዎች በሙሉ በድምር (lot) ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢው ይሆናል፡፡ በዚህ መስፈርት መሠረት ለሁሉም እቃዎች ዝርዝር ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  13. የጨረታ መክፈቻው ቀን በእለቱ ከስራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ፡- 0331118629 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በደሴ ከተማ አስ/ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
MSF Belgium Ethiopia Mission Tender for Supply of Various Types of Stabilizers (Tender Ref. ET121 &...

READ MORE