Tender Detail

Tender Details

  • Company አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል
  • Address አሰላ ልዩ ቦታው አርሲ ዪኒቨርሲቲ ንብ እርባታ አለፍ ብሎ ፡ አሰላ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 022-2-38-29-90
  • Website
  • Deadline05 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲከስ ማስልጠኛ ማዕከል ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ ግዥ በሃገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡- 001/2017

 

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲከስ ማስልጠኛ ማዕከል ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ ግዥ በሃገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በውድድሩ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በዘርፉ በአቅራቢነት ዝርዘር ላይ በድረ-ገጽ የተመዘገቡ፤ ክሊራንስና ሌሎች ዶከመንቶች ካሉ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል አሰላ ልዩ ቦታው አርሲ ዪኒቨርሲቲ ንብ እርባታ አለፍ ብሎ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ
  • ሎት 001 ደንብ ልብስ 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ቴክኒካል ኦሪጅናል እና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እንዲሁም አንድ ፋይናሽያል ኦሪጅናል እና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በተለያዩ የታሸጉ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል በመቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  1. ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማስለጠኛ ማዕከል አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት የሚጠቀሙት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል ባዘጋጀው ዶክመንት ላይ በመሆኑ ዋጋቸውን የሚሞሉት በዚሁ ሰነድ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
  3. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 10% በማስያዝ አሸናፊነታቸው በተገለጻላቸው በ7 ቀን ውስጥ ውል ካልገቡ ለጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ስነ-ስርዓት ባይገኙ የጨረታው ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  5. የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከል ለአሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ሲረከብ ብቻ ክፍያ የሚፈጽም ሲሆን ለግዢው ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ ማዕከሉ የማይፈጽም ይሆናል፡፡
  6. የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲከስ ማስልጠኛ ማዕከል የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የእቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  8. አንድ ተጫራች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጨረታ ከመክፈቻው ሰዓት በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ያልያስያዘ ተጫራች በጨረታው አይወዳደርም፡፡
  10. የርክክብ ቦታ የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከል አሰላ ይሆናል ፡፡

 

ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 022-2-38-29-90

 

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል

 

Save Tender