አማስ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አ.ማ 5L ሚኒባሶች ብዛት 1 ፤ ሞተር ብስክሌት ብዛት 3፣ አይሱዙ የደረቅ ጭነት (NPR) ብዛት አንድ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
አማስ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
አማስ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አ.ማ 5L ሚኒባሶች ብዛት 1 ፤ ሞተር ብስክሌት ብዛት 3፣ አይሱዙ የደረቅ ጭነት (NPR) ብዛት አንድ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1ኛ. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት 22 ቅርንጫፍ ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ከመክሊት ህንፃ ጀርባ አማስ ዋናው መ/ቤት ከጠዋቱ 3፡00-10፡00 ሰዓት የተዘጋጀውን ሠነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመግዛት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።
2ኛ. ማንኛውም ተጫራች መግዛት የሚፈለገውን ተሽከርካሪ አያት ጨፌ ቁጥር 1 ኮንዶሚኒየም ድረስ በመሄድ ማየት ይችላሉ።
3ኛ. ተጫራቾች የሚሸጡት ተሸከርካሪ የመነሻ ዋጋ 25% በሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማስያዝ አለባቸው።
4ኛ. ተጫራቾች ከተቋሙ ከሚገዙት የጨረታ ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ዝርዝር ላይ የሚሰጡትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በትክክል በመሙላት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5ኛ. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ከላዩ ላይ ሙሉ ስሙንና አድራሻ በመፃፍ እስከ 28/5/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተጠናቆ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ከዚህ ሰዓት በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ። ጨረታው በዚሁ በተዘጋበት ዕለት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
6ኛ. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው ያሸነፉትን ተሸከርካሪ ሙሉ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ በመክፈል ንብረቱን የማንሳት ግዴታ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን ድርጅቱ ጨረታውን ሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘውን ገንዘብ ለተቋሙ ገቢ የሚያደርግ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል።
7ኛ. ተቋሙ ስለ አሻሻጩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ስልክ ቁጥር :- 0116-66-20-12/09-11-11-68-72/09-38-11-12-13
አድራሻ ፡- ከጎላጎል ወደ መገናኛ መንገድ ከመክሊት ህንፃ ጀርባ
አዲስ አበባ
አማስ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አ.ማ
