የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ የደንብ ልብሶችንና ጨርቆችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Hawassa University College of Medicine and Health Sciences (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር :- HU/CSH/NCB/Yedenb Libs/06/06/2017 BY
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ የደንብ ልብሶችንና ጨርቆችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ፤ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ድረ-ገጽ /web-site/ ላይ የተመዘገቡ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼከ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሠነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በኮሌጁ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡40 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንሰስ ኮሌጅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር :- +251-4-62-12-01-20
ፋክስ ቁጥር ፡- +251-4-62-20-87-55
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
