የነቀምቴ ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ በጎ አድራጎት ማህበር ከተቀናጀ የጤናና ልማት አገልግሎት ድርጅት ጋር እያከናወነው ባለው ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪን መከላከል ድጋፍና እንክብካቤ ፕሮጀክት ሥራ ከጀንዋሪ 1/2024 - ዲሴምበር 30/2024 ዓመታዊ በጀቱን ኦዲት ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
የነቀምቴ ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ በጎ አድራጎት ማህበር
የኦዲት ሥራ አገልግሎት
ጨረታ ማስታወቂያ
የነቀምቴ ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ በጎ አድራጎት ማህበር ከተቀናጀ የጤናና ልማት አገልግሎት ድርጅት ጋር እያከናወነው ባለው ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪን መከላከል ድጋፍና እንክብካቤ ፕሮጀክት ሥራ ከጀንዋሪ 1/2024 - ዲሴምበር 30/2024 ዓመታዊ በጀቱን ኦዲት ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ተወዳዳሪ ኦዲተሩ/ዋ
1. ከፌዴራል ወይም ከክልል የተሰጠው የኦዲተርነት የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ
2. የዘመኑ ግብር የተከፈለበትና የታደሠ ማስረጃና የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ቲን ቁጥር
3. ተወዳዳሪው/ዋ ከበጎ አድራጎት ማህበሩ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ/ች/ ለጨረታው የሚጠቅሙ ለማቅረብ የሚችል፤ የኦዲት ምርመራ ሥራው የሚከናወነው ነቀምት ከተማ ቡርቃ ጃቶ ክፍለ አስተዳደር ውስጥ መሆኑን አውቆ ቦታው ድረስ ቀርቦ ለመሥራት የሚፈልግ፤ ተወዳዳሪው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስረጃዎቹንና ለሙያ ሊከፈለው የሚገባውን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በአድራሻችን በመላክ መወዳደር ይቻላል፡፡
የጨረታው ሳጥን ከ10 ቀናት ቆይታ በኋላ የሚዘጋ ሲሆን የሚከፈተው በተዘጋ ማግሥት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተወዳዳሪው/ዋ/ ወይም ወኪሉ በተገኙበት ይሆናል፡፡
በጎ አድራጎት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
የነቀምቴ ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ በጎ አድራጎት ማህበር
