በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀርቡ ከተማ በ2017 በጀት አመት ለከተማው አገልግሎት የሚውል የመንገድ ዳር መብራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀርቡ ከተማ በ2017 በጀት አመት ለከተማው አገልግሎት የሚውል የመንገድ ዳር መብራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21/5/2017 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ ሀ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት አባይ ባንከ አንደኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የሚፈለገውን የዕቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቶቹ ለየብቻ በመለየት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒአ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀናት ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ በየሎቱ 10% በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም (እቃ) መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በየሎቱ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሰነድን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አባይ ባንከ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በ 22/5/2017 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰአት ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ዕለት የማይገኙ ከሆነ በሌሉበት ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን እና ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል።
- መ/ቤቱ ካሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ካሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው፤ አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም።
- አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ የማቅረብ ግዴታ ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ተጫራች ኦርጅናል እቃዎችን የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን እቃዎቹን የምንቀበለው በሚመለከተው ባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ሀርቡ ከተማ አስተዳደር ግ/ፋ/ን/አስ/ አባይ ባንክ አንደኛ ፎቅ ላይ በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 0335520883 /0921031272 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ ፡- በማንኛውም ሁኔታ የተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በሚከፈትበት ሰዓት የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
