የጎጎታ ኬር የከምባታ ጠምባሮ ዞን ሕዝቦች ልማት ማህበር እ.አ.አ. የ2024 በጀት ዓመት ሂሳብ ምርመራ ለማስደረግ አገልግሎት ሰጪዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጎጎታ ኬር የከምባታ ጠምባሮ ዞን ሕዝቦች ልማት ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጎጎታ ኬር የከምባታ ጠምባሮ ዞን ሕዝቦች ልማት ማህበር እ.አ.አ. የ2024 በጀት ዓመት ሂሳብ ምርመራ ለማስደረግ አገልግሎት ሰጪዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ፡-
- ተጫራቾቹ በዘርፉ አግባብነት ያለው ሕጋዊ ፍቃድ ያለው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
- ቲን ሰርተፍኬት ያለው፣
የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የውጭ ኦዲተሮች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ (7) ቀናት የሚሰሩበትን ዋጋ ዝርዝር እና የሚጨርሱበትን ቀን በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የሂሳብ ምርመራ የሚደረግባቸው ሠነዶች ብዛት
- የአንድ ዓመት ጠቅላላ ገቢ ብር 45,850,469.34
- የአንድ ዓመት ጠቅላላ ወጪ 26,355,556.48
- የቦክስ ፋይል ብዛት 26
ድርጅቱ አሸናፊውን በጽሑፍ የሚያሳውቅ መሆኑን እየገለጽን፤ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ አምስት ኪሎ ናዝሬት እስኩል አጠገብ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር ዋና ቢሮ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 716 በሚገኘው የድርጅታችን ቅ/ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ማስገባት ትችላላችሁ።
ስልክ ቁጥር :- 091 197 1339 / 090 482 9031/ 093 722 1455
የጎጎታ ኬር የከምባታ ጠምባሮ ዞን ሕዝቦች ልማት ማህበር
