Tender Detail

Tender Details

  • Deadline28 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Used Items

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማይንቀሳቀሱ እና አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች (የቧንቧ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የእጅ መሳሪያዎች ሌሎች ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ያገለገሉ የሻወር ገንዳዎች፣ የሽንት ቤት መቀመጫዎች፣ ያገለገሉ የእቃ ማጠቢያ ሳህኖች፣ ያገለገሉ የሻወር ቦይለሮች እና የሻወር ማሞቂያ መቆጣጠሪያዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ያገለገሉ ፕሪንተሮች፣ ኮምፒውተሮች እና የኮምፒውተር ቶነሮች እንዲሁም ያገለገሉ መደርደሪያዎች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ቁጥር ል/ቅ/ 01/2017

 

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማይንቀሳቀሱ እና አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች (የቧንቧ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የእጅ መሳሪያዎች ሌሎች ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ያገለገሉ የሻወር ገንዳዎች፣ የሽንት ቤት መቀመጫዎች፣ ያገለገሉ የእቃ ማጠቢያ ሳህኖች፣ ያገለገሉ የሻወር ቦይለሮች እና የሻወር ማሞቂያ መቆጣጠሪያዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ያገለገሉ ፕሪንተሮች፣ ኮምፒውተሮች እና የኮምፒውተር ቶነሮች እንዲሁም ያገለገሉ መደርደሪያዎች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

      1. ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ኢሬቻ ማክበሪያ ጎን ወይም ኢ ሲኤ በታቸኛው በር ፊት ለፊት ሳልኮስት በሚገኘው በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመምጣት በቅርንጫፉ ሥር በሚገኙ የማይንቀሳቀሱ እና አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ግንባታ እቃዎች (የቧንቧ እቃዎች ፤ የእጅ መሳሪያዎች ያገለገሉ ሻወር የሽንት ቤት መቀመጫዎች፣ የእቃ ማጠቢያ ሳህኖች፣ የሻወር ውሀ ማሞቂያ ቦይለሮች እና የሻወር፣ ማሞቂያ መቆጣጣሪያዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች ያገለገሉ ፕሪንተሮች ኮምፒውተሮች እና የኮምፒውተር ቶነሮች እንዲሁም ያገለገሉ መደርደሪያዎች ዝርዝር የያዘውን መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00/ አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
      2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙትን ንብረቶች ብቻ የጥቅል ዋጋ እንዲሁም የንብረቱን ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ በማሣየት ድምሩን በአሃዝ ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፋይናንስ ገቢ አሰባሰብ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሣጥን ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ባሉት ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ በየምድቡ ከተቀመጡት ዕቃዎች መካከል ተጫራቹ የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች ብቻ መርጦ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
      3. የዕቃው /ንብረቱ ዋጋ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሠነዱ ላይ ዋጋው የተጨማሪ እሴት ታክሱና ጠቅላላ ድምሩ በሠንጠረዡ መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
      4. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
      5. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሠነዶቹ ላይ በማስፈር በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፤
      6. ተጫራቾች ለሚገዙት የግንባታ የቢሮ የጽህፈት የእጅ እና የተለያዩ እቃዎች ላይ በጥቅል 2,524.00./ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሃያ አራት ብር / ብቻ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከመከፈቱ በፊት ሣጥኑ ውስጥ አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የሚዘጋጀው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
      7. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሳጥኑ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን መከፈት አያስተጓጉልም፤
      8. ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኃላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
      9. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
      10. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ውጤት ለአሸናፊ እና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በኮርፖሬሽኑ የውስጥ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሠሌዳና በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረጋል፤
      11. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ውጤቱ በልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰሌዳ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
      12. በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፤
      13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፤ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ካላነሱ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% / 1/1000/ በየቀኑ እየተሠላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል፤ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ለቅርንጫፉ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸው ይሠረዛል።
      14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
      15. ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) በፊት መሆን አለበት።
      16. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በፌዴራል  ቤቶች  ኮርፖሬሽን  የልዩ  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት

 

Save Tender