በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2017 በጀት አመት ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2017 በጀት አመት ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፍርቶች የሚያሟሉና በየንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ሆነው መጫረት የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች
- ህጋዊ የታደስ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው
- የግዥው መጠን ከብር 200000/ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና ከዚያም በላይ ከሆነ 9 በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገበ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላል፡፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 /መቶ/ ብር በመክፈል እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 የሰነድ ክፍያ በመፈጸም የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ /ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ስነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በተቀመጠዉ በየሎቱ ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋት 3፡30 /ሶስት ሰዓት ተኩል ድረስ/ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 3፡31 /ሶስት ከሰላሳ አንድ ተዘግቶ 4፡00 /አራት ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎችን ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙሊያው ላይ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸዉን እቃዎች እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ 06 ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ 1/2003 እና ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጡ ሰርኩላሮች መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ሆኗል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
