በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ጥቅም ላይ የሚውሉ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የተለያዩ የኮምፒውተር እቃዎች፣ የተለያዩ የወርክ ሾፕ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን እና አነስተኛ የእጅ መገልገያ መሳሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Defence University (የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ)
የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልፅ የጨረታ መለያ ቁጥር ፡- ኢ/መ/ዩ/ኢ/ኮ 02/2017
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ጥቅም ላይ የሚውሉ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የተለያዩ የኮምፒውተር እቃዎች፣ የተለያዩ የወርክ ሾፕ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን እና አነስተኛ የእጅ መገልገያ መሳሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለ2017 ዓ.ም የሚያገለግል የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑን የግብር መክፈላችሁን የሚያረጋግጥና በመንግስት ግዢ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ በመጨረሻም በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ላይ የተመዘገቡትን ማስረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ስም በተከፈተው በኢት/ንግድ/ባንክ ቁጥር 1000640119377 ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫይስ በማምጣት በኮሌጅ ግዥ ዴስክ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ የድርጅታችሁን ህጋዊ ማህተምና ፊርማ በማስቀመጥ መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ አድርገው ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢ/መ/ዩ ኢ ኮሌጅ ውስጥ በሚገኘው ግዥ ዴስክ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለቀረቡት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ከታወቁ የፋይናንስ ተቋማት የተሰጠ በሲፒኦ ወይም በዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ዴስክ ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ ለአፈፃፀም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ቢሾፍቱ በቀጥታ ስልክ ቁጥር፡ 011-4-33-84-00 የውስጥ መስመር 276 እና 274 ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
