ዓባይ ባንከ አ.ማ ሆቴል ተከራይተው የሆቴል አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ያላቸውን እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ የባንኩ ንብረት የሆነውን በጎንደር ከተማ ቀበሌ 03 የሚገኘውን ቋራ ሆቴል ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Abay Bank S.C (ዓባይ ባንክ አ.ማ)
የሆቴል ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር : AB/PPM/05/14/2024-25
ዓባይ ባንከ አ.ማ ሆቴል ተከራይተው የሆቴል አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ያላቸውን እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ የባንኩ ንብረት የሆነውን በጎንደር ከተማ ቀበሌ 03 የሚገኘውን ቋራ ሆቴል ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር/ቢሮ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር መለያ ሰርተፍኬት፣ ታክስ ክሊራንስ፣ የድርጅቱን ፕሮፋይልና ተቋማዊ ብቃት የሚያረጋግጥ መረጃ እንዲሁም የስራ ልምድ እና ሌሎችም ተዛማጅ ዶክመንቶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከማንኛውም ባንክ በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቢያንስ ለ90 ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሆቴል ኪራይ የሚያስገቡት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ (Price Validity Date) መግለፅ አለባቸው፡፡ ይህም ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ከ90 ቀን ማነስ የለበትም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር በዓባይ ባንክ ቅርንጫፎች በመክፈል እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ባምቢስ አካባቢ ኖክ ፊት ለፊት ከሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌከስ 8ኛ ፎቅ ዓባይ ባንከ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ወይም ዓባይ ባንከ ጎንደር ዲስትሪክት ቢሮ በመቅረብ ከታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ሆቴሉን ማየት የሚፈልግ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 03 በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ዓባይ ባንከ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሆቴል ስራ የሚያስፈልጉትን የሆቴል እቃዎች በራሳቸው ማሟላት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557-16 14/011-557-17-60 የባንኩን ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ዓባይ ባንክ አ.ማ
