በአሮሚያ ክልል ምሥ/ሸዋ ዞን ኦለንጭቲ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ በ2017 በመደበኛ በጀት የጽ/መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የስልጠና እቃዎችና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምሥ/ሸዋ ዞን ኦለንጭቲ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአሮሚያ ክልል ምሥ/ሸዋ ዞን ኦለንጭቲ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ በ2017 በመደበኛ በጀት የጽ/መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የስልጠና እቃዎችና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም እጩ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ከነዋጋ ማቅረቢያው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በመለየት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም እጩ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ለማቅረብ አስቀድሞ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ አቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 ለእያንዳንዱ ሠነድ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦለንጭቲ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ከቀረበው አጠቃላይ የግዢ ዋጋ መስሪያ ቤቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጠቅላላ የግዥ ዋጋ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከሆነ 2% ተቀናሽ ይሆናል፡፡
- እጩ ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ከፋይ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- እያንዳንዱ እጩ ተጫራች የንግድ መለያ ቁጥር (TIN number) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ካሽነፈርት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ከመ/ቤቱ ጋር ውሉን ከፈረመ በኋላ ዕቃውን ለቦሰት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት በራሱ ማጓጓዣ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ሥ.ቁ
0989500407
0912863007
0912320010 ይደውሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምሥ/ሸዋ ዞን ኦለንጭቲ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ
