የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአራቱ በተመረጡ ቦታዎች (Conformity Assessment Service, ISO Management System Training Service, Equipment Calibration Service, እና የውስጥ ኦዲት አገልግሎት በISO/IEC 17025 2017 መሰረት) ለኢንፍላይት ኬተሪንግ አገልግሎት አክሬዲቴሽን ግምገማ ስራዎችን የሚሠራ ድርጅት (ተቋምን) በግልፅ ጨረታ መጋበዝ ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡ SSNT-T520
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአራቱ በተመረጡ ቦታዎች (Conformity Assessment Service, ISO Management System Training Service, Equipment Calibration Service, እና የውስጥ ኦዲት አገልግሎት በISO/IEC 17025 2017 መሰረት) ለኢንፍላይት ኬተሪንግ አገልግሎት አክሬዲቴሽን ግምገማ ስራዎችን የሚሠራ ድርጅት (ተቋምን) በግልፅ ጨረታ መጋበዝ ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ፍላጎት ያላቸውና ብቁ የሆኑ አገልግሎት አቅራቢዎችን በሙሉ መጋበዝ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች አክሬዲቴሽን ግምገማዎች አገልግሎት እንዲያቀርቡ ሥልጣን ባለው አካል በአገር ውስጥ የተመዘገቡበት ለ2017 ዓ.ም የሚያገለግል እና ፈቃድ አቅራቢው የተሰማራበትን የሥራ መስከ የሚያመለከት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብም ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በማንኛውም የመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ብቁ መሆናቸውንና ከግብር ዕዳ ነፃ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T520 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ጨረታው የሚቆየው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-4918
አሰፋ ኃይሉ
ኢ-ሜይል : Assefah@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
