በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ2017 በጀት ዓመት በፑላችን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ ጽ/ቤቶች አገልገሎት የሚሰጡ ኤሌክትሮኒክስ /ኢንተራክቲቭ ፍላት ፓናል/ እና ዲጂታል ሚዛን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን ከምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2017
በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ2017 በጀት ዓመት በፑላችን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ ጽ/ቤቶች አገልገሎት የሚሰጡ ኤሌክትሮኒክስ /ኢንተራክቲቭ ፍላት ፓናል/ እና ዲጂታል ሚዛን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን ከምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን አራት ኪሎ በሚገኘው የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ በዋና ስራ አስፈጻሚ የፋ/ አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ 9ኛ ፎቅ 902 ቁጥር የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው (አስረኛው) የስራ ቀን ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት እና በማሸግ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዋና ስራአስፈፃሚ የግዥ ቡድን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በየዘርፉ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ከጨረታው ይሰረዛል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የአጠቃላዩን ብር 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
- በጥቃቅን ተደራጅተው በዘርፉ ለተሰማሩ ተጫራቾች የተገለጹትን ቁሳቁሶች የአምራችነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ይህ ካልሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0111-26-54 40
የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን
